የባለሥልጣን መ/ቤቱ ሰራተኞች የወርቃማ ሰኞ የማለዳ መርሃ-ግብርን አካሄዱ
• ስለ ተቋሙ የሰራተኞች የሥራ ሰዓት አከባበር ዙሪያ ላይም ውይይት ተደርጓል
**********************
(ት/ማ/ባ ህዳር 22/2018ዓ.ም)፡-የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን የበላይ የሥራ ኃላፊዎችና የማዕከል ሰራተኞች የእውቀት ሽግግርና የልምድ ልውውጥ የሆነውን የወርቃማ ሰኞ የማለዳ መርሃ-ግብር በተቋሙ መሰብሰብያ አዳራሽ አካሂደዋል፡፡
በእውቀት ሽግግርና የልምድ ልውውጥ መርሃ-ግብሩ ላይ የስታንዳርዳይዜሽን ዝግጅት አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል እና ድጋፍ ዳይሬክተር አቶ ሐጎስ ካህሳይ ስለ ‹‹ቅን መሪ›› ምንነት አስመልክቶ ሰነድ አቅርበዋል፡፡


በሰነዱም ላይም ስለ ቅን መሪ ምንነት፣ ባህሪያትን ከባለሥልጣን መ/ቤቱ ስልጣንና ተግባር እንዲሁም ራእዩ ጋር በማዛመድና ምሳሌዎችን በመጥቀስ ለማዕከሉ ሰራተኛ አብራርተዋል፡፡
መሪነት ከራስ እንደሚጀምርና ቅንነት ያለው መሪ በሰራተኞች መካከል መቻቻል እንዲፈጠር ማድረግ፣ የእያንዳንዱን ስራ ማበረታታት ስራውን ባለማጣጣል፤ ምስጋና በመስጠትና በማነቃቃት ለአንድ አላማ እንደቆሙ ማድረግ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡
በመቀጠልም በባልስልጣን መ/ቤቱ የሰው ሀብት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግርማ ኢዶሳ የተቋሙ ሰራተኞች የሥራ ሰዓት አከባበርና እየተወሰዱ ባሉት እርማጃዎች ዙሪያ ተቋሙ ያለበትን ሁኔታ ሰነድ አቅርበው ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
በመጨረሻም የባለሥልጣን መ/ቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ኤልያስ ዘርጋ ባስተላለፉት መልዕክት ለተቋሙ ራእይ ማሳካት ከታች እስከ ላይ ያለ ሰራተኛ በቅንነትና በታማኝነት በመቀናጀት በአንድ ዓላማ የተቋሙን ራእይ ለማሳካት መጣር ይገባዋል ብለዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ
https://linktr.ee/aatma1
ነፃ የስልክ መስመር
696ን ይጠቀሙ