ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራተን እንደቀጠለ ነው፡፡
*************************
(ት/ማ/ባ/ የካቲት 18/2018 ዓ.ም)፡- በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን የአቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከክፍለ ከተማዋ ትራፊክ ፖሊስ፣ ትራንስፖርት ቅ/ጽ/ቤት፣ ፖሊስ፣ ደንብ ማስከበር እና አሽከርካረ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤቶች ጋር በመቀናጀት በትራንስፖርት ዘርፉ በሚታዩ ደንብ መተላለፎች ጉዳዮች ላይ የተጠናከረ ተግባር እየፈጸመ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ሰሞኑን በቅንጅት የተሰራውም በክፍለከተማው ህገ-ወጥ የፓርኪንግ እንቅስቃሴን የማስቆም፣ ከህብረተሰቡ የተነሱ የመንገድ አስተዳደር ጥያቄዎችን የመመለስ፣ በትራንስፖርት ዘርፉና በትራፊክ አንቅስቃሴው ዙሪያ የሚታዩ ደንብ መታላለፎችን መስመር የማስያዝና በተሽከርካሪዎች ላይ ድንገተኛ የቴክኒክ ምርመራ በማድረግ እንዲስተካከሉ የማድረግ እንደሆነ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
በእዚሁ እንቅስቃሴም 168 በደንብ ተላላፊነት፣ 13 አሽከርካሪዎች ደግሞ የተሸከርካሪ ጉድለት እያለበት በማሽከርከራቸው የእርምት እርምጃ እንደተወሰደባቸው የሚያመለክተው ይኸው መረጃ በክፍለከተማው በቅንጅት የሚከወነው ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል፡፡

The branch office continues to work in coordination with stakeholders.
*************************
(T/M/B/ February 18/2018 A.D.):- The Addis Ababa Traffic Management Authority Akaki Qaliti Branch Office announced that it is working intensively on issues of violations in the transport sector in coordination with the city's Traffic Police, Transport Department, Police, Law Enforcement and Motor Vehicle Licensing and Control Authority.

The recent joint efforts include stopping illegal parking activities in the city, answering questions raised by the community about road management, marking the lines of violations in the transport sector and traffic activities, and conducting emergency technical inspections on vehicles to ensure that they are corrected.
He also announced that the same information, which indicates that 168 drivers were fined for driving while impaired, and 13 drivers were fined for driving while impaired, will continue to be actively involved in the coordination of activities in the city.



