(ት/ማ/ባ ህዳር 20/2018 ዓ.ም):_
በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በተያዘው በጀት ዓመት 2ኛ ሩብ ዓመት በፈጣን ምላሽ አምጭ እቅድ መሰረት የ5ኛ ሳምንት የስራ አጻጸም ሪፖርት ላይ የበላይ አመራሮች፣ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች፣ የማእከል የስራ ሃላፊዎችና የቅርንጫፍ ጽ/ቤት የቁጥጥርና የፖርኪንግ ዳይሬክተሮች በተገኙበት ተገምግሟል።
ተቋሙ በ2ኛዉ ሩብ አመት በልዩ ሁኔታ ውጤት ለማስመዝገብ በእቅድ የያዛቸውን የአብይና ንዑስ ተግባራት አፈጻጸም፣ በቁጥጥር እና በፓርኪንግ አስተዳደር ያሉትን ስራዎች፣ የቅሬታና አቤቱታ አፈታት ስርዓት፣ አገልግሎት አሰጣጥና ምቹ የስራ አካባቢን መፍጠር፣ እንዲሁም የገቢ አሰባሰብ እና የመስክ እይታ ሪፖርትን በፎቶና በቪዲዮ አስደግፈው ያቀረቡት የስታንዳርዳይዜሽን ዝግጅት፤ አግልግሎት አሰጣጥ ክትትል እና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ብሩክ በለጠ ናቸው።
የተግባራቱ ፈፃሚዎችም በቀረበው ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ በየሳምንቱ የተግባራት መሻሻሎች ቢኖርም በቀጣይ ሳምንታት በሪፖርቱ የተጠቆሙትን አንዳንድ ክፍተቶችን በመሙላት የተሻለ ውጤት እንደሚያስመዘግቡ ጠቁመዋል።

የበላይ አመራሮችም ፈጣን ምላሽ አምጪ እቅድ ወደ ተግባር ሲለውጥ መድበኛ ሰዓትን ብቻ መጠቀም ሳይሆን በተጨማሪ ጊዚያቶችም በመስራት ከሂደት አልፎ ለውጥና ውጤት መታየት አለበት ብለዋል።
በመጨረሻም ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳ በቀሪ ሳምንታት ለውጦችንና ጥንካሬዎችን ይዞ መቀጠል፣ ተጠያቂነትን ማስፈን፣ ክፍተቶችን ማረም፣ ክዋኔ ላይ ማተኮር፣ ተደራራቢ ውጤቶችን ማስመዝገብ፤ ብለው ያስቀመጧቸውን አቅጣጫዎች ተሳታፊዎች በሙሉ ድምፅ በመቀበል መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።
ለበለጠ መረጃ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ

https://linktr.ee/aatma1
ነፃ የስልክ መስመር
696ን ይጠቀሙ



