over 315 commercial shops built in the corridor development

Today, we have handed over 315 commercial shops built in the corridor development to the tenants who were working on rent in the kebele and various commercial buildings.
Our administration has provided two options to the residents who were previously working on rent in the government-owned kebele and various commercial buildings in our city, and they have given them the opportunity to organize themselves in shares and enter their commercial shops and start working, or else they have given them the opportunity to rent shops provided by the government.

Most of them have continued their business by renting the shops built and provided by the government, and there were many who chose to organize themselves in shares and build their commercial shops and trade. Since they were not able to build among those who were allowed to organize themselves in shares and take over the land and build, they have been asking for another option in various discussion forums.
Therefore, our administration has decided to solve the problem; for the residents who have been displaced due to the corridor development, riverside development and redevelopment works; He has allotted 315 modern commercial shops built in various parts of the city in the corridor development.
May the Creator bless Ethiopia and its people!
ዛሬ በኮሪደር ልማት የተገነቡ 315 የንግድ ሱቆችን፣ በቀበሌና በተለያዩ ንግድ ቤቶች በኪራይ ሲሰሩ ለነበሩ የኮሪደር ልማት ተነሺዎች በዕጣ አስተላልፈናል።
በከተማችን ከዚህ ቀደም የመንግስት የቀበሌና የተለያዩ ንግድ ቤቶችን ተከራይተው ሲሰሩ ለነበሩ ነዋሪዎች አስተዳደራችን ሁለት አማራጮችን አቅርቦ እንደየምርጫቸው በአክሲዮን ተደራጅተው ወደ ንግድ ሱቃቸው ገብተው ሥራ እንዲጀምሩ፣ ይህ ካልሆነም መንግስት የሚያቀርብላቸውን ሱቆች ተከራይተው እንዲሰሩ እድል ሰጥቶ ነበር።
አብዛኛዎቹ መንግስት ገንብቶ ያቀረብላቸውን ሱቆች ተከራይተው ንግዳቸውን የቀጠሉ ሲሆን፣ በአክሲዮን ተደራጅተው ወደ ንግድ ሱቃቸው ገንብተው ለመነገድ የመረጡም በርካቶች ነበሩ። ከእነዚህ በአክሲዮን እንዲደራጁና መሬት ተረክበው እንዲገነቡ ከተፈቀደላቸው ውስጥ የመገንባት አቅም በማጣታቸው በተለያዩ የውይይት መድረኮች ሌላ አማራጭ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ ቆይተዋል።
በመሆኑም አስተዳደራችን ችግሩን ለመቅረፍ፤ በኮሪደር ልማት፣ በወንዝ ዳርቻ ልማት እና በመልሶ ማልማት ሥራዎች ምክንያት ለተነሱ ነዋሪዎች፤ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች በኮሪደር ልማቱ የተገነቡ 315 ዘመናዊ የንግድ ሱቆችን በዕጣ እንዲተላለፉላቸው አድርጓል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!

Leave a comment



Copyright 2025 TMA © All Rights Reserved
Email Address: aartma2011@gmail.com
Phone Number: 696 TMA Free Line  AND  0116672386

Developed by Tewodros Kemal  (@.tk)