Unique, radiant, international-standard LED traffic signs and indicators have been installed in the city.

በከተማዋ በዓይነታቸው የተለዩ አንፀባራቂ የኤል.ኢ.ዲ አለም አቀፍ የትራፊክ ምልክትና ማመላከቻዎች ተተከሉ
*******************
(ት/ማ/ባ የካቲት 10/2018 ዓ.ም)፡- የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅንት ባለስልጣን ተጀምረው በተጠናቀቁትና አሁንም እየተሰሩ ባሉ የኮሪደር ልማት ፕሮጅክቶች እና በተለያዩ መጋጠሚያዎች፣ አደባባዮች፣ እግረኛ መሻገሪያ /ዜብራዎች/፣ባቡር መሻገሪያዎች እና መሰል ቦታዎች ላይ የኤል.ኢ.ዲ አለም አቀፍ ምልክትና ማመላከቻዎች እየተከለ ነው፡፡
ተቋሙ ሰሞኑን ተሰርቶ በተጠናቀቀው በቦሌ- ኡራኤል ኮደር ልማት እና በከተማዋ ሌሎች መንገዶች በ24/7 የሥራ መርህ አንፀባራቂ የኤል.ኢ.ዲ መብራት ያላቸው ዘመናዊ አለም አቀፍ የትራፊክ ምልክት እና ማመላክቻዎችን ተክሏል፡፡
የተተከሉትም የፍጥነት መገደቢያ፣ የፍጥነት ወሰንና የአሽከርካሪዎች ማቆሚያ ፓርኪንግ ስፍራዎች፤ ማቆም የሚከለክሉ አስገዳጅና መረጃ ሰጪ ምልክቶችና ማመላከቻዎቹም ናቸው፡፡
በባለስልጣን መ/ቤቱ የመንገድ ደህንነት ምህንድስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንጂነር መርጋ ሰፈራ አንፀባራቂ ኤል.ኢ.ዲ ምልክትና ማመላቻዎች ጠቀሜታ አስመልከተው እንዳሉት የከተማዋ አሽከርካሪዎች ከአደጋ የሚጠብቁና ፍሰትን ያሚያሳልጡ፤ የትራፊክ ምልክቶችን የማክበር እና በህጉ ተገዝቶ የማሽከርከር ልምድ ማዳበር አለባቸው፡፡
ሰሞኑን እየተተከሉ ያሉት በዓይነታቸው ልዩ የሆኑት እነዚሁ አንፀባራቂ ኤለል.ኢ.ዲ መብራት የተገጠመላቸው ምልክቶች ጎላ ጎላ ያሉ ስለሆኑ የአሽከርካሪውን እይታ ከመጨመራቸውም በላይ ትኩረት ሰጥተው አንዲያሽከረክሩ ይረዳቸዋል ያሉት ኢንጂነር መርጋ ምልክቶቹ ቀድሞ ከነበሩት የተለዩ በመሆናቸውም ከደህንነት ባለፈ ለከተማዋ ውበት አሰተዋጽኦ እንዳደረጉ ገልጸዋል፡፡
በቀጣይም በከተማዋ የመንገድ መብራት በሌለባቸው መንገዶች ላይ እና በሌሎችም ስፍራዎች በስፋት ለመትከል ዝግጅታቸውን እንዳጠናቀቁና አሽከርካሪዎችም የሚተከሉ የትራፊክ ምልክቶችን በማክበር እና በትራፊክ ህጉም በመገዛት ራሳቸውንና ወገኖቻቸውን ከትራፊክ አደጋ እንዲጠብቄ አሳስበዋል፡፡
Unique LED traffic signs and signals installed in the city
********************
(T/M/B February 10/2018 AD):- The Addis Ababa Traffic Management Authority is installing LED traffic signs and signals at various intersections, squares, pedestrian crossings (zebras), railway crossings and similar places in the corridor development projects that have been started and completed and are still being implemented.
The institution has installed modern LED traffic signs and signals with 24/7 working principle in the recently completed Bole-Urael Coder Development and other roads in the city.

The installed speed limit, speed limit and parking areas for drivers; Mandatory and informative signs and signals prohibiting stopping are also included.
Engineer Merga Sefera, Director of the Road Safety Engineering Directorate of the Authority, emphasized the importance of LED signs and signals, saying that drivers of the city should be aware of dangers and avoid traffic; respect traffic signs and drive according to the law.

The unique LED signs that are being installed recently are more visible and help drivers pay attention and drive more efficiently, Engineer Merga said, adding that the signs are different from the previous ones and have contributed to the beauty of the city in addition to safety.
He further stated that they have completed preparations to install street lights on roads and other areas of the city that do not have them, and urged drivers to protect themselves and their loved ones from traffic accidents by respecting the posted traffic signs and obeying traffic laws.

Leave a comment



Copyright 2025 TMA © All Rights Reserved
Email Address: aartma2011@gmail.com
Phone Number: 696 TMA Free Line  AND  0116672386

Developed by Tewodros Kemal  (@.tk)