The task force has been working to reduce the cost of living and prevent illegality.

The task force has been working to reduce the cost of living and prevent illegality.
The Market Stabilization, Illicit Trade Control and “Ethiopia Addis Ababa Tamert” Task Force reviewed the work done to ensure stable trading during the Eid al-Fitr holiday and to prevent product shortages and unreasonable price increases during the upcoming Easter holiday, as well as to prevent illegality.


According to Addis Ababa City Deputy Mayor and Task Force Chairman Ato Jantrar Abay, who led the discussion, the work done to increase supply during the Eid al-Fitr holiday is encouraging, and the leadership will work diligently to prevent product shortages and unreasonable price increases during the upcoming Easter holiday.
The members of the task force, for their part, said that they have made sufficient arrangements to ensure broker-free trading by establishing ties with the regions to prevent supply shortages and unreasonable price increases.
Finally, Honorable Ato Jantrar Abay urged the government to work diligently to prevent supply shortages and illegal activities during the upcoming Easter holiday by developing a concrete plan to solve the problem, ensuring supply, preparing locations, monitoring supply, and ensuring that there are no brokers at shopping centers.

ግብረ ሀይሉ የኑሮ ውድነትን በመቀነስና ህገወጥነትን በመከላከል ተጨባጭ ስራ መሰራቱ ተገለጸ።
የገበያ ማረጋጋት፣ ህገወጥ ንግድ ቁጥጥር እና “ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ታምርት” ግብረ ሀይል በኢድ አልፈጥር በዓልን የተረጋጋ ግብይት እንዲካሄድ የተሰሩ ስራዎችን እና በመጪው የፋሲካ በዓል የምርት የአቅርቦት እጥረትና ያልተገባ የዋጋ ጭማሬ እንዳይኖር እንዲሁም ህገወጥነትን ለመከላከል የሚሰሩ ስራዎችን ገምግሟል ።
ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የግብረ ሀይሉ ሰብሳቢ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደገለጹት፣ በኢድ አልፈጥር በአል አቅርቦቱን ከፍ ለማድረግ የተሰራው ስራ አበረታች መሆኑን ገልጸው ከፊታችን የሚከበረውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ የምርት እጥረትና ያልተገባ የዋጋ ጭማሬ እንዳይኖር አመራሩ በትኩረት ይሰራል ብለዋል ።
የግብረ ሀይሉ አባላት በበኩላቸው የአቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር ከክልሎች ጋር ትስስር በመፍጠርና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እንዳይፈጠር ከደላላ ነጻ የሆነ ግብይት እንዲኖር በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
በመጨረሻም በመጪውን የፋሲካ በዓል የተረጋጋ ግብይት እንዲከናወን የአቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠርና ህገወጥነትን ለመከላከል ችግር ፈቺ ተጨባጭ እቅድ ማቀድ፣ አቅርቦትን ማረጋገጥ፣ ቦታዎችን ማዘጋጀት፣ አቅርቦትን የሚያሳልጥ ቁጥጥር ማድረግ እንዲሁም የግብይት ማእከላት ላይ ደላላ እንዳይኖር በመከታተል በትኩረት እንዲሰሩ የተከበሩ አቶ ጃንጥራር አባይ አሳስበዋል።
[yarpp]

Leave a comment



Copyright 2025 TMA © All Rights Reserved
Email Address: aartma2011@gmail.com
Phone Number: 696 TMA Free Line  AND  0116672386

Developed by Tewodros Kemal  (@.tk)