Warning to Drivers‼️
***************
Chevron/yellow and white V-shaped road markings are mandatory markings on roads to guide drivers; highlight curves or road dividers and determine safe distances for drivers. They also improve visibility, warn of lane changes and reduce the risk of collisions.
However, we have found that drivers are driving on these mandatory markings during inspections and inspections.
Therefore, drivers should be aware that the markings are for your own safety and that you should obey the law and avoid additional fines!

የጥንቃቄ መልእክት ለአሽከርካሪዎች
************
ቼቭሮን/በብጫና ነጭ ቀለም በV ቅርጽ የተቀቡ የመንገድ ላይ ቀለም ቅቦች አሽከርካሪዎችን ለመምራት፤ ኩርባዎችን ወይም የመንገድ አካፋዮችን ለማጉላት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የአሽከርካሪዎችን ርቀት ለመወሰን በመንገዶች ላይ የተቀቡ አስገዳጅ የቀለም ቅብ ናቸው። በተጨማሪም ዕይታን ያሻሽላሉ፣ የአሰላለፍ ለውጦችን ያስጠነቅቃሉ እንዲሁም የግጭት አደጋዎችን ይቀንሳሉ።
ይሁን እንጂ በእነዚህ አስገዳጅ በሆኑ ቀለሞች ላይ አሽከርካሪዎች እየተጓዙበት መሆኑን በጥቆማና በተደረገ የቁጥጥር ወቅት ደርሰንበታል፡፡
በመሆኑም አሽከርካሪዎች የተጠቀሰው ቀለም ቅብ ከማንም በላይ ራሳችሁን የሚጠቅም መሆኑን ተገንዝባችሁ ህግ አክብሩ ከተጨማሪ ቅጣትም ራሳችሁን እንድትታደጉ ሲል ባለስልጣን መ/ቤቱ ያሳስባል!

