wd_asp id=1

The office has officially launched the website that has been developed by internal capacity

Officially launched the official website of the authority, which the office lacked in capacity. The website, which was developed by internal staff and approved by the Addis Ababa Innovation Technology Development Office, was officially launched today. The website was introduced in the presence of senior officials and employees as one of the social media options that the office uses to make the activities of the city's traffic comfortable and ensure its safety accessible to the public. Speaking at the opening of the program, the director general of the authority office, Ato Kbebewu Mideksa, said that the authority office is one of the 13 institutions in the reform process. Using it is a process that requires time He also pointed out that it is important to officially launch a website. Head of Addis Ababa Innovation Technology Development Office Mr. Grum Abtewu said that as a city, the website is the most important to make services efficient and accessible. Therefore, the authority pointed out that the office has started working by developing a website on its own to make the work it does accessible to the public and provide services easily. Therefore, they thanked the experts who created the website on their own initiative and announced that their responsible institution will provide technical assistance and training to ensure the security of the website and make it work continuously. The institution's information technology expert Mr. Tbebe Daniel explained the purpose of the website, information exchange process, customer service; The method of discussion on the website, advertising works, the features of the website and the use of language that make them special, the consideration of the disabled, the option to receive customer suggestions online and other uses were presented in detail. Members and employees of the institution to the expert who made the website; They thanked the head of the Information Technology Directorate and requested that it be properly implemented. Finally, Tewodros Kemal, an expert who created the website on his own initiative, was presented with a certificate of recognition. The website of the authority is: https://aatma.gov.et/

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በዉስጥ አቅም ያለማዉን ድረ-ገጽ በይፋ ስራ አስጀመረ
*************,,
(ት/ማ/ባ ህዳር 12/2017 ዓ.ም) ፡- የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በራስ አቅም በውስጥ ሰራተኞች የተሰራዉን እና በአዲስ አበባ ኢኖቪሽን ቴክኖሎጅ ልማት ቢሮ የፀደቀዉን ድረ-ገጽ በዛሬው እለት በይፋ ስራ አስጀመሯል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የከተማውን ትራፊክ ፍሰት ምቹ ለማድረግና ደህንነቱንም ለማረጋገጥ የሚያከናዉናቸዉን ተግባራት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ከሚጠቀምባቸዉ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መካከል ድረ-ገጹን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሠራተኞች በተገኙበት አስተዋውቋል፡፡
በመረሃ-ግብሩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበዉ ሚደቅሳ እንደገለጹት ባለስልጣን መ/ቤቱ በከተማዋ በሪፎርም ሂደት ዉስጥ ካሉት 13 ተቋማት መካከል አንዱ ነው:: የዚህም ዋና አላማ አገልግሎት አሰጣጥን ፈጣንና ዉጤታማ ለማድረግ ነዉ፡:
ስለሆነም አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ ለማድረግ የቴክኖሎጅ ዉጤቶችን መጠቀም ጊዜው የሚጠይቀው ሂደት ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ለህብረተሰቡ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት የተቋሙን ድረ-ገጽ በይፋ ስራ ማስጀመር ወሳኝ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የአዲስ አበባ ኢኖቬሽን ቴክኖሎጅ ልማት ቢሮ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ግሩም አብተዉ በበኩላቸው እንደ ከተማ ልዩ ትኩረት የሚሰጠዉ አገልግሎትን ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ ድረ ገጽ ዋነኛዉ ነዉ ብለዋል፡፡
በመሆኑም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በራሱ አቅም ደረ-ገጽ በማልማት ወደ ስራ በመግባቱ የሚሰራቸዉን ስራዎች ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግና አገልግሎትን በቀላሉ ለመስጠት እንደሚያስችለው ጠቁመዋል፡፡
በመሆኑም ድረ-ገጹን በራስ ተነሳሽነት ያለሙትን ባለሙያዎች አመስግነዉ የተሰራዉን ድረ-ገጽ ደህንነቱን አስጠብቆና ቀጣይነት ባለዉ መልኩ እንዲሰራበት አደራ ያሉት ሃላፊዉ ተቋማቸውም ቴክኒካል እገዛና ስልጠናዎችን እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡
የተቋሙ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ አቶ ጥበበ ዳኒኤል የድረ-ገጹን ጥቅም አላማ፣ የመረጃ ልዉዉጥ ሂደት፣ የደንበኞች አገልግሎት; በድረ-ገጹ ላይ የመወያያ መንገድ፣ ማስታወቂያ ስራዎች፣ የድረ-ገጹ ባህሪያት እና ለየት የሚያደርጉትን የቋንቋ አጠቃቀም ፣አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ማድረጉ፣ የተገልጋይን ጥቆማ በኦንላይን ለመቀበል ያለዉ አማራጭና ሌሎችንም መጠቀሚያዎች በዝርዝር አቀርበዋል፡:
በመቀጠልም የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የበላይ አመራሮች፣ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች፣ተሳታፊ ባለድርሻ አካላትና የተቋሙ ሰራተኞች ድረ_ገጹን ለሰራው ባለሙያ; ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ዳይሬክቶሬት ሃላፊና ባለሙያዎች ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በቀጣይም በአግባቡ ተግባረዊ እንዲሆን ጠይቀዋል::
በመጨረሻም ድረ-ገጹን በራስ ተነሳሽነት ያለማዉ ባለሙያ ቴዎድሮስ ከማል ከምስጋና ጋር የእዉቅና የምስክር ወረቀት ተበርከቶለታል ፡፡
የባለስልጣን መ/ቤቱ ድረ_ገጽ:
https://aatma.gov.et/ መሆኑም ታውቋል::



Leave a comment



Copyright 2025 TMA © All Rights Reserved
Email Address: aartma2011@gmail.com
Phone Number: 696 TMA Free Line  AND  0116672386

Developed by Tewodros Kemal(@EaseWD)

Back
Telegram