wd_asp id=1

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በዕቅድ አፈጻጸም እና በትራፊክ አደጋ ንጽጽር ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ግምገማዊ ውይይት አካሄደ ******...

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በዕቅድ አፈጻጸም እና በትራፊክ አደጋ ንጽጽር ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ግምገማዊ ውይይት አካሄደ
************
(ት/ማ/ባ ጥር 21/2017 ዓ.ም)፡- የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን የጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወር ዕቅድ አፈጻጸም እና በትራፊክ አደጋ ንጽጽር ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ግምገማዊ ውይይት በጽ/ቤቱ በዛሬው ዕለት አካሄደ፡፡

የዕቅድ አፈጻጸሙን ሪፖርት ያቀረቡት የጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የመንገድ ደህንነት ግንዛቤና ደንብ ማስከበር ዳይሬክቶሬት አቶ ገዛኽኝ ታምሩ እንደተናገሩት በስድስት ወር ውስጥ በተከናወኑ ተግባራት ከተገኙ ውጤቶች መካከል በመንገድ ላይ የሚከናወኑ ሕገ ወጥ ኩነቶችን መቀነስ መቻሉ፣ በሃይማኖታዊ በዓል አከባበር ወቅት ምዕመናን ላይ የሚደርሰውን የትራፊክ አደጋ መቀነስ፣ በተለይ በትምህርት ቤቶች አካባቢ የእግረኞች የመንገድ አጠቃቀም መሻሻሉ ፣ አደባባይ ላይ የሚቆሙ ተሽከርካሪዎችን በማንሳት የትራፊክ መጨናነቅን መቅረፍ መቻሉ፤በአጠቃላይ በመንገድ ተጠቃሚዎች ዘንድ የሕግ ተገዥነት መሻሻል ማሳየቱ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
እንደ አቶ ገዛኽኝ ሪፖርት ከባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት መሠራቱ፣ አልኮል ጠጥቶ በማሽከርከር፣ በእግረኛ እና በፍጥነት ቁጥጥር ላይ በፕሮግራም እየተሠራ መሆኑ በጠንካራ ጎን ከሚነሱ መካከል የሚጠቀሱ ሲሆን የባለሙያ አለመሟላት እና የግብዓት እጥረት ካጋጠሙ ችግሮች መካከል መሆናቸው ተመላክቷል፡፡ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ተብለው ከተቀመጡት ከባለድርሻ አካላት ጋር የበለጠ ተቀናጅቶ መስራት፣ ከአቻ ተቋማት ጋር የልምድ ልውውጥ በማድረግ ተሞክሮን መጠመርና ማስፋት እንዲሁም የትራፊክ ፍሰትና ደህንነትን የሚያሻሽሉ ምልክቶችን በጥናት በመለየት ማሻሻል የሚሉት ይገኙባቸዋል፡፡

በውይይቱ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ የጉለሌ ክፍለ ከተማ የትራፊክ የሕዝብ ግንዛቤና የአባላት ሙያ ማሳደግ ማስተባበሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ደምስ ማሞ እንደተናገሩት በዕቅዶች ላይ ተቀናጅቶ መሥራት ውጤታማ ያደርጋል ብለዋል፡፡ አቶ ደሱ አሰፋ ከአዲስ አበባ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት እንደተናገሩት የጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከባለድርሻ አካላት ጋር መሥራት በመቻሉ የትራፊክ መጨናነቅ እንዲቀንስ አድርጓል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም በቀረበው ሪፖርት ላይ ባለድርሻ አካላቱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን የጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሕይወት ታደሠ እንደገለፁት ውይይቱ ዓላማውን ያሳካ ሲሆን የተገኙ ውጤቶችን አጠናክረን በማስቀጠል በቀጣይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተባብረን እንሠራለን፡፡





Leave a comment



Copyright 2025 TMA © All Rights Reserved
Email Address: aartma2011@gmail.com
Phone Number: 696 TMA Free Line  AND  0116672386

Developed by Tewodros Kemal(@EaseWD)

Back
Telegram